ፕሮፌሽናል የሞባይል ጥገና ጥቅማጥቅሞች እና መረጃዎች
ስልክዎ ውሃ ውስጥ ከገባ ወዲያውኑ ማጥፋት አለብዎት። ባትሪው የሚወልቅ ከሆነ አውጥተው በደረቅ ጨርቅ ይጥረጉት። በፍፁም በፀጉር ማድረቂያ (Hair dryer) ለማድረቅ አይሞክሩ፤ ምክንያቱም ሙቀቱ ውስጣዊ ክፍሎችን ሊያቀልጥ ይችላል።
የስልክዎን ባትሪ ቻርጅ ሲያደርጉ ሁልጊዜ 100% እስኪሞላ አይጠብቁ። ከ20% እስከ 80% ባለው ክልል ውስጥ ማቆየት የባትሪውን ዕድሜ በአጅሩ ያረዝመዋል። እንዲሁም ጥራት የሌላቸው ቻርጀሮችን ከመጠቀም ይቆጠቡ።
ከበስተጀርባ (Background) የሚሰሩ ብዙ አፕሊኬሽኖችን ይዝጉ። ስልኩ ቻርጅ እየተደረገ ከባድ ጌሞችን አይጫወቱ። ይህ በውስጣዊ የቦርድ ክፍሎች ላይ ጫና ይፈጥራል።